ሪፖርተር ልብ ሊገዛ ነው
http://ethiopianreporter.com/index.phpበኢትዮጵያዊነታችን እንድንኮራ አድርጉን!!
- Wednesday, 05 October 2011 09:34
በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኮራ አድርጉን!!
ሲል በቃ! ማለትም እየደፈረ ያ ብ ር ራ ራ ል >
....... በነገራችን ላይ የመብታችን ጉዳይ ስለሆነ ‹‹እንድንኮራ አድርጉን›› የሚል አባባልም መባል አልነበረበትም፡፡ መብትህ ነው፤ መብቴ ነው የሚባልበት አጀንዳ ነውና፡፡ እንድንኮራ አድርጉን የምንለው ሕገመንግሥቱን አክብሩልን፤ በሕገመንግሥቱ ተገዙ ማለታችን ነው፡፡በተለይ በአሁኑ ጊዜ ያለው እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ስትበደል አቤት የምትልበት አካል አለመኖሩ ነው፡፡ በስም ማለታችን አይደለም፡፡ በስም በበጀትና በሰው ኃይል አቤቱታ ሰሚ፣ እንባ ተቀባይ የሚባሉና የበላይ አካል የሚባሉ አሉ፡፡ ችግሩ ግን የነሱ በር የሚከፈተው ለፈለጉት ግለሰብ እንጂ ለሁሉም ዜጋ አይደለም፡፡ ለፈለጉት በራቸው ይበረገዳል፤ ለማይፈልጉት ደግሞ ይቸነከራል፡፡ ለሁሉም ዜጋ እኩል የሚከፈት በርና ልብ ጠፍቷል፡፡
ይህ ሁኔታ በአስቸኳይ መቀየር አለበት፡፡ ተጨማሪ ጩኸት፣ አላስፈላጊ ደም መፍሰስ አያስፈልግም፤ አይጠይቅም፤ ሕገመንግሥትን በተግባር ላይ ማዋል ብቻ ነው፡፡ በቃ!
መንግሥት ሕገመንግሥቱን ያከብር፤ ይተግብር፤ ሕዝብም የሚነካኝና የሚበድለኝ የለም ብሎ ይተማመን፤ መንግሥትም ግዴታውን ይፈጽም፤ ይሥራ፤ እኛም በኢትዮጵያዊነታችን እንኩራ!
*
No comments:
Post a Comment