Berhane-Aymero

Sunday, 5 June 2011

የመልስ ጋጋታ፤ የዜና ፋብሪካ

የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ! 

ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን! 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።

በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን ፤ መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ፦ ማከማቻ

 -ኤርትራን እወራለሁ

-አባይን ገድባለሁ

-ግብጥን ነክሻለሁ

-ሱዳን እሄዳለሁ
      ሰላም መጥናለሁ

-ሱማሌ  እቆያለሁ።

-ዋጋ  መቆ ጣጠር
ትቻለሁ ፡ ለቃለሁ

-ካቶሊክ ሆኛለሁ ፤ 
ነጋዴ አግብቼያለሁ

- ይቅርታ ብያለሁ፤
ደርግን እፈታለሁ።

 (ይኀ  ሁሉ፤)

እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ  ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
ባህር ማዶ ያለውን፤ በየፈረንጅ ባንኩ።

(ላለ ማለት  ሽር ጉዱ!)

*
ሌቱ እስኪነጋ ለት
ቀን እስኪወጣ ለት
ያገሬ ሰው እንደሁ
ተኝ ሲሉት ተኛለሁ
ቁም ሲሉት ቆማለሁ።

እኔ ግን እነሁ
አድንቁ ይግረማችሁ  ፤
ቀኔ የሞላ ለት
 ክጫካ ወጥቼ፤
አሜሪካን ወዶኝ
እንግሊዝ ዶልቼ፤
ከተማ ገብቼ፦
ሙሉ ሃያ ዓመት ገዛሁኝ
የምሥራች በሉኝ።
ነገም ዛሬም እኔ ፤ አርባ እሞ ላለሁ፤
እከርማለሁ ገና  ከንጉሥ እበልጣለሁ፤
ቤን አሊ ጋዳፌ ሙባረክ አይደለሁ
ባስራ ሁለት ቢላ መብላት ተክኛለሁ።

እንደኔ ዓይነት ምላስ፤ 
                     ከሰንበር የሚለይ
ባሳብ በትካዜ፤
ባገር በወንዜም ላይ፤
                ኣንድም ቀን አይታይ፤
መለስ ዘና ዘና፤ ደሞም፤
ካስፈለገም
የሚል ቆጣ ቆጣ
የሚያስደነግጥም በጣቶች ቆረጣ፤
                   ሃያ ምላስ አለኝ
በመላው አፍሪቃ፤
                ፍጡም ወደር የለኝ።
ለሁሉም መልስ ያለው፤
                         መለስ እባላለሁ
ባባቴ ዜናዊ ፤ 
የዜና ፋብሪካ፦ 
                      ወሬ እወልዳለሁ
ዕጡብ ድንቅ በሉኝ፤ 
                           ዘላለም ኖራ ለ ሁ።
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ! 

ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን! 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን። 
በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን ፤ መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ፦ ማከማቻ
 *
ሞልትዋል፤ተትረፍርፍዋል፤

ይቀጥላል ገና
የ መለስ፦ የመልስ ጋጋታ-- የፋብሪካ ዜና።

No comments:

Addis Tiwlid 2012 - The New Generation 2012

Berhane-Matemia

The Synthesis

LibraryThing

Legacy politics: When two people quarrel rejoices the third – to rule over them… (up to the 20th century)

Visionary politics: When two people come together rejoices the third – to join them in their Human Empathy…(… 21st century ….)

*

Human DIGNITY:

21st century is the era of Liberation Movements for Human Dignity, encompassing all other Movements, to make them superfluous – non-dogmatic, non-religious and non-ethnic with the great Common Collective Will for Human Empathy!

11 0220 11 - EGYPT's Dignity Day, the Landmark for a radical break with all Tyrannies!

Thanks to

Tunisia -The Heroic Pioneer of Freedom!

2011 - The Dignity Year for Tunisia