ልቀጥል ልቀጣጥል ላስተውል በውኔ
ይሞላልኝ እንደሁ፤እስኪያልፍልኝ ቀኔ።
-
እንቁ፡ ጣጣሽ ይሉ፤ ነጋልን ፈካልን የአደዩ አበባ፤
አውዳመት ቢመጣ፣ ቢወዱት፤ቢወደት፣ መስከረም ቢጠባ
ታዲያስ ምን ይጠበስ፤ የኔ አይደል የደራው፤
ከፈለግህ ደግሞ ይባስብህ ብለው ፤
ሳር ቅጠሉን ሁሉ አሸባሪ ብለው
እንግዲያስ ወዳጄ፤ በየትኛው ታምር መነጫነጭ ልተው፤
-
እንዲያው ፤ አልፎም ተርፎ፤
ወዳኛውን ባየው፣ ባምነው ብዘከረው
ለዚህኛው ምድር፤ አልበጀኝ፤ ሆዴንም፣ ልቤንም አልሞላው።
ደሞስ- ሃይማኖቱ ሁሉ የኖሩበት ሃገር በክብር ተሳስበው፤
ሼክ አይቀር ፓፓሱ ይባሉበት ዘመን ሆነና እንደ ሰው
ምንፈሱም ርቆናል ምድር ባዶውን ነው፡፡
-
ደግመን ድጋግመንም፤ጠብበን፤ ነገሥነው፡
ገዛነው እያሉን፤እነሱም እነዚያም ቢተረክላቸው፤
እንዲያው ከፍ ፤ክፍፍ ያለውም ሰም፣ ባፋፍ ባፋፉ ላይ ቢስየምላቸው፤
የኔን ቤትስ ፤ ተዉት፤ ቢሞላ ባይሞላ፡ቢነከር በእዳ
እነደ መነደራቸው፤ የጨርቃ ጨርቅ ገቢያ
ቸርችረው በተኑት ላሞራው ቅኝ ገዢ፤ ባህር ማዶ ወዲያ ።
*
እንዲህ ሆኖ እኮ ነው፣ መስከረም ሲጠባ፤ይሚያመናጭቀው፤
ከንገዲህስ በቃን እኒንም እኒያን ውጊድ እንበላቸው።
ቢሆንም ባይሆንም፣ የሆነም ሆኖ ፤የማይሆንም ቢሆን፤
ህይወት ትልቃለች፤ ብታምርም፣ ብትመርም፣ ብትቀጥን፤
እንደ የወጋችን፤ እንደየምነታችን፣
*
ሲሆ ን ቢሆንማ ንጭንጭ ማጉረምረሙን ትተን
ነበር እንደሰዉ ከንቁ ጣጣሽ አልፈን ማክበር ዳመራውን!
No comments:
Post a Comment