..." Go, go ahead, arrest me, you can arrest me too; like my fellow friends, I have talked to Amnesty International and Human rights Organsisations, if that should be a criminat act!"
(My free translation from the Amahric; on the Press Conference by Dr. Gidada, former Ethiopian President, now UDJ Chairman in the opposition)
*
*
እንቁ፡ ጣጣሽ ይሉ፤ ነጋልን ፈካልን የአደዩ አበባ፤
አውዳመት ቢመጣ፣ ቢወዱት፤ቢወደት፣ መስከረም ቢጠባ
ታዲያስ ምን ይጠበስ፤ የኔ አይደል የደራው፤
የኔማ ጥኔ ነው፤ በሚሊዮን መንደር ምዓት ከመከራው።
*
ረሃብና ችግር ማምረቱ አንሷቸው!
ቆሽቴ እየበገነ ሁሉን ሳሳልፈው፡
ከፈለግህ ደግሞ ይባስብህ ብለው ፤
ሳር ቅጠሉን ሁሉ አሸባሪ ብለው
እውነት ከዳሚውን ኣፉን አስለጉመው
ተጫዋችም ሳይቀር ቁምነገር ከልክለው፤
በደበበ እሸቴ፦ ፈገግ ብለን እንኳን ጊዜን እንዳንገፋው፤
ተስፋና ፈገግታ እንዳይኖር ደንግገው፤
አርዓያ፦ ለነጻነት ድፍረት እንዳይሆኑ ነፍገው
ጎበዝ! እስክንድር ፤ አንዷለምን አይቶ፦ ልቡን እንዳይሞላ ፈርተው
መላ ሃገሩን ሁሉ፦ ቆርጠዋል ሊያደርጉት፦ ወህኒ ቤት ቀዝቃዛው!
ከህሊና ቢስ ሌላ፦ ኧረ ለመሆኑ ፦ዛ ሬ ! ማን አል የሚሞቀው?
*
ሲሆ ን ቢሆንማ ንጭንጭ ማጉረምረሙን ትተን
ነበር እንደሰዉ ከንቁ ጣጣሽ አልፈን ማክበር ዳመራውን!
በርታ ጎበዝ ፤ የርትዕ ያገር የወገን ልጅ
መንፈስ ካንተ ይሁን ህዝቡንም ይፈርጅ፤
ግድ የለም ፦አይቀርም ይደርሳል
ልብ ትካዜንም አልፎ ፦አንድ ቀን ይሞላል
ህዝብን ያጥለቀልቀዋል፤
አዎ አይቀርም፤ ንቁ ጣጣሽ ብሎ ዳመራን ያከብራል::
ዋ ብሎ አወይ ጉድ ይሆናል!
ያች ቀን ስትበራ
ወዮለት አሞራ
ዕብሪት ያሳበደው የቁራዎች አውራ!!
No comments:
Post a Comment