Berhane-Aymero

Friday, 23 September 2011

The Secret Drone and The Victim



አቤት እንካበእንካ
ጉድ ነው አሜሪካ


አይ!! ያገሬ ልጅ ዛሬ፤ ብቅ  የምትለው ባፍላ
እንደ እስክንድሩ፦እንደ አንዷለም አይነት፦ልብህም የሞላ፦

አደራህን በርታ፤ ግን አትሁን ተላላ።

የለም የሚያግዝህ፤  ከወገንህ ሌላ
ቡሽ ቢሄድ፦ ቢጠራ፦ቢመጣ ኦባማ፦ ቢትተካ ይስሙላ
በነጻነት ምኞት በዴሞክራሲ ማላ
አ ባ ይ ነው፤  ወስላታ ነው  ሁላ!

አንተን ወህኒ ጥሎ፤ ይላል እንካበእንካ
የምላስ ወዳጁ  ያ ማዶ አሜሪካ።
   *
 
*
ቀለሙ እንኳን ሳይደርቅ ያፈ ጮማይትዋ
ሚሲስ ክሊንተንዋ አፈ ቀላጢዋ፤
የተደረሰላት በነጻነት ፍቅርዋ፦

ጉድ ሳያድር ወጣ፤
ማን ይሁን ወዳጁ፤ ማን ይቆይ ባላንጣ።

ይህን አጋጣሚ ማን ያምናል ማ ይሙት
አንተን ተደራድሮ ለወህኒ ሲዶልት፤
*
U.S. builds secret drone base in Ethiopia
Washington Post: Sept. 22, 2011
*
ምስጢረ አይሮፕላን መስፈሪያ ተሰጥቶት
ሰንብቶ ለመኖር ጠላትህን ባርኮት፤
ስም ለአንተ አወጣልህ፦ አሸባሪ ብሎ፦ ስትሞግት ላርነት።

አሸባሪ እራሱ፤ ቀላማጅ አለቃው ወሮ በላን አቅፎት
በዚም በዚያ ቢላ መስሎ ሲበላበት፦
እሪ በል ያሰኛል፤ ባንክሮ ስናየው፤ አርጎን አሻንጉሊት

ኧረ በቃን በቃኝ፤ እንበላቸው ይህንም እንያንም፦ 
በ ራ ሳ ችን እ ን ቁ ም 
ሁ ሉ ም አይሆ ኑንም።

ይ፦ አስመሳይ ወዳጆች
የመብት ተቆርቅዋሪ፤ አሜሪካን ብሎ የኛ ተሟጓቾች
ድሮስ ማን ሆኑና አህያ ያስነዱት፦የመለስ አንጋሾች!!!!

ይልቅ  ሀ   እንበልበት፦ መላ  እንፈልግበት
የክፉዎች ሽብር፤ ድንገት የሚፈጥራት
የምትረባ ሽብር፤ ውበት ሲወለዳት
እንዴት በምን አርጎ፤ ታግሶ፤  ታሽቶ እንደሚከስታት፤
ይሻላል እውነቱን በጽሞና ማጥናት
አንድ ሁለት እንበል፤ ስለ ቅኔ ማህሌት፦
ስለ ሽብር ዕውቀት፦፦
*
ልብ በል
ይባላል
ስለ ብር ዕወቅት

ስለ ብር ዕወቅት (1
ተቀኝታ  ነበር አፍቃሪ ላፍቃሪው
ስለ ዕውሩ ፍቅር ስለሚጋርደው፦
ዓይን የተፈጠረው ሁሉን ለማየት ነው
አንተን አይቶ ሌላ አላይ አለ ምነው! "
እሱዋስ አፍቃሪ  ናት
ፍቅር ያሳበዳት
ምርምር መገንዘብ  ዕውቀት የከጀላት
ሽብር ፈጠራት
ፍቅር ያሳበዳት

አላወቀች ዛሬ መከልከሉን ማየት።
*
እንደ ንገሩማ     የግል ት፦
ብትሰማ     ባትሰማ     አል   ንገርዋት
ኣንድም ሶስትም ይኩን   ምርጫ አላት፤
ብት     ባት     አል   ንገርዋት
የፍቅር  ቅኝቱ  ላልተገለጸላት



 / አሃዱ በግዕዝ -  ካልደፈረ    ሰማ፤
መች ይሻዋል ጥራት፤
መች ይመኛል ብቃት፤

/ ሲክተል በካብዕ   - ካል           ማ፤
መች ይሻዋል ጥራት፤
መች አነሰው ብቃት፤

/ ሲያበቃው በሳድስ -  ካልደፈረሰማ፦
መች ይሻዋል ጥራት፤
በድካም ነው ብቃት፤

ንጉሥ ትመርቂ ወደሽ ነው ኮማሪት፤
አንቺም እሱም እስዋም፦
--እኔም እኒያም ሁሉም፤
-- የወዲያው ቀርቶብሽ፦
ለዚህ የበቃችሁት!

ህግዋ ነው  የፍጥረት፤
                !
አሽብሮ አሸብሮ፦ አሸ ብሮ ብቃት!

(! ቅኝት ለቀጠለው፦ ሽብር - አሸ ብሮ አሸብሮ - ያሸበርቃል / አሸበረቀ  ይሆ ናል!  ለልፈለገው --ብር ይሸ ብራ አሸብሮ ይቀራል !)
1)      I take Chaos“  for  the correct translation of  “Shibir“ -  

 

No comments:

Addis Tiwlid 2012 - The New Generation 2012

Berhane-Matemia

The Synthesis

LibraryThing

Legacy politics: When two people quarrel rejoices the third – to rule over them… (up to the 20th century)

Visionary politics: When two people come together rejoices the third – to join them in their Human Empathy…(… 21st century ….)

*

Human DIGNITY:

21st century is the era of Liberation Movements for Human Dignity, encompassing all other Movements, to make them superfluous – non-dogmatic, non-religious and non-ethnic with the great Common Collective Will for Human Empathy!

11 0220 11 - EGYPT's Dignity Day, the Landmark for a radical break with all Tyrannies!

Thanks to

Tunisia -The Heroic Pioneer of Freedom!

2011 - The Dignity Year for Tunisia